ዜናዎች እና ዝግጅቶች
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን ገመገመ::
July 10, 2026
ዜናዎች
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን ገመገመ:: ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን ከማኔጅመንት አባላትና ከመላው ሰራትኞቹ ጋር በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ገምግሟል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ በበጀት ዓመቱ በነበረው ቅንጅታዊ አሰራር አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል የመላው ሰራተኞችን ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።
መድረኩ የያንዳንዱን ፈጻሚ ሚና በመፈተሽ ለቀጣይ ዓመት ዕቅድ ስኬት አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
የነባር ፕሮጀክቶች የጀመመሪያ ምዕራፍ የግንባታ ስራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው፣ በበጀት ዓመቱ የተሻለ የጥሬ ግብዓት ወደ ፓርኩ በብዛትና በጥራት መቅረቡ፣ ተጨማሪ ኢንቨስተሮችን መሳብ መቻሉና የሁሉም ዘርፍ ስራዎች በአፅንኦት መከናወናቸው በግብርና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ሀገራችን ላስቀመጠችው ግብ ስኬት ኮርፖሬሽኑ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አመላካች መሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቁሟል።
በመርሃግብሩ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረኩ በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ተጨማሪ ዜናዎች
ተጨማሪ ዜናዎችን ለማግኘት በፌስቡክ ይከተሉን
ዕለታዊ ዝመናዎችን፣ ፎቶዎችን እና ማስታወቂያዎችን እዚህ ከመታየታቸው በፊት በፌስቡክ ገጻችን ላይ እንለቅቃለን። እንዳያመልጥዎ ይከተሉን።
ሲዳማ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በፌስቡክ ይከተሉ