跳转到主要内容
Hawassa City, Sidama Regional State
የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን ገመገመ::
新闻

የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን ገመገመ:: ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም, ሲዳማ ኢ/ፓ/ል/ኮ, ሀዋሳ

‎የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን ከማኔጅመንት አባላትና ከመላው ሰራትኞቹ ጋር በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ገምግሟል።
‎የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ በበጀት ዓመቱ በነበረው ቅንጅታዊ አሰራር አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል የመላው ሰራተኞችን ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።
‎መድረኩ የያንዳንዱን ፈጻሚ ሚና በመፈተሽ ለቀጣይ ዓመት ዕቅድ ስኬት አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
‎የነባር ፕሮጀክቶች የጀመመሪያ ምዕራፍ የግንባታ ስራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው፣ በበጀት ዓመቱ የተሻለ የጥሬ ግብዓት ወደ ፓርኩ በብዛትና በጥራት መቅረቡ፣ ተጨማሪ ኢንቨስተሮችን መሳብ መቻሉና የሁሉም ዘርፍ ስራዎች በአፅንኦት መከናወናቸው በግብርና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ሀገራችን ላስቀመጠችው ግብ ስኬት ኮርፖሬሽኑ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አመላካች መሆናቸው በሪፖርቱ ተጠቁሟል።
‎በመርሃግብሩ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረኩ በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
关注我们的 Facebook 获取更多新闻

我们会在 Facebook 主页上发布日常动态、照片和公告,通常比网站更新得更早。关注我们,不错过任何消息。

在 Facebook 上关注 SIPDC
SIPDC 虚拟助手
咨询投资与合作问题
您好!我是 SIPDC 虚拟助手。您可以咨询投资、我们的服务,或贵机构如何与我们开展合作。
本助手为自动问答工具,非真人客服。